የአብክመ ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለሆነም ከላይ የተጠቀሰውን ዕቃ ለማቅረብ የሚችሉና ህጋዊ የአቅራቢነት ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች ሁሉ በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ እና ከብር 200,000 ብር /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ አና በላይ ለሚጠይቁ ግዥዎች (የቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ብር 450,000 /አራት መቶ ሃምሳ ሽህ ብር/ ብቻ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተመሰከረለት ቼክ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት አብክመ ገቢዎች ቢሮ ባሕርዳ ር ቢሮ ቁጥር 313 ኤሌክትሮኒክስ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ ሰነዱን በመግዛት የነጠላ ዋጋ እና ጥቅል ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 313 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ቅዳሜ እስከ 6:30 ጨምሮ ማስገባት የሚችሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 313 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡
- አስራ ስድስተኛው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ማንኛውንም ወጭ ራሱ ችሎ ለቢሮው አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች ያስረክባል፡፡
- ቢሮዉ በማንኛውም ሰዓት ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
አድራሻችን፡- ባሕር ዳር ቀበሌ 16 ሜድሮክ ጀርባ እና የድሮው ዶ/ር ፍሬው የነበረው የአሁኑ ዶ/ር አዲሱ ክሊኒክ ፊት ለፊት ስልክ ቁጥር 058 226 57 65 ወይም 058 226 61 71 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአብክመ ገቢዎች ቢሮ

