ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
56

የወልድያ ከተማ ውሃ አገልግሎት (ድርጅት) የአንድ ዓመት ማለትም  የ2017 ዓ.ም  በጀት ዓመት ሂሣብ በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች በጋዜጣ አወዳድሮ ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን በማሟላት በጨረታ ለመወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. መ/ቤቱን (ድርጅቱን) ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ ደረጃ ያለው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር ከፍለው ፈቃዱን ያደሱ፡፡
  3. በሂሣብ ምርመራው (ኦዲት) ተግባር ላይ የሚያሳትፋቸውን ባለሙያዎች ብዛት CV፣ የትምህርት ደረጃ፣ የሥራ ልምድ ወዘተ … ከእያንዳንዱ ባለሙያ ጋር የተያዘ (የተገባ) የቅጥር ውል ስምምነት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የበጀት ዓመት ሂሣብ ኦዲት ለማድረግ በሰጠው ጠቅላላ ዋጋ ላይ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረ (ሲፒኦ) 2 በመቶ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የሚያከናውኑትን ተግባር በተመለከተ ከድርጅቱ ጋር ዝርዝር ውል ለመፈረም ፈቃደኛ ሊሆን ይገባል፡፡
  6. ተጫራቾች ስለ መልካም ሥራ አፈፃፀማቸው ከአሁን በፊት የሂሣብ ምርመራ (ኦዲት) ካደረጉባቸው ድርጀቶች የተፃፈላቸውን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  7. የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ተመዝጋቢ ከሆነ፣ የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት (ቲን) እና ሌሎች ለጨረታው የሚጠቅሙ ማስረጃዎችን የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  8. የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) ወልድያ ከተማ ውሃ አገ/ት መ/ቤት (ድርጅት) ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ፡፡
  9. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በጽ/ቤታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናሉንና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  10. ተጫራቾች የእያንዳንዱን ዓመት ኦዲት ሥራ የኦዲት ሥራው የሚከናወንበትን የሥራ ዝርዝር እና በመጨረሻ የሚያቀርቡት የኦዲት ሪፖርት ይዘት እንዲሁም የሚወስድባቸውን ጊዜ በተመለከተ የድርጊት መርሃ ግብር (ማስኬጃ ውል) በማዘጋጀት በታሸገ ኢንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. የጨረታው ቀን ጋዜጣው ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ላይ የጨረታ ሣጥኑ ታሽጎ በዚሁ ቀን በ 3፡30 ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 4 ጨረታው ይከፈታል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ ከአስፈለገ በስልክ ቁጥር 033 431 07 99 /033 431 12 23 በEmail gechmog@gmail.com ፋክስ 033 331 15 72 በመጠቀም መጠየቅ ይችላሉ፡፡

መ/ቤቱ (ድርጅቱ) የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የወልድያ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here