በምሥራቅ ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ቤት ፍርድ ቤት ሃገረ ሰላም ወረዳ ፍ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት አመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ ሎት 4 አነስተኛ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 5 ህትመት እንዲሁም ሎት 6 የቢሮ እቃዎች ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሰለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በተራ ቁጥር ከ1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ማለትም ቲን ነበር፣ ንግድ ፈቃድ እና በውክልና የሚስሩ ከሆነ የውክልና ወረቀት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር ከፖስታው ውጭ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙትን እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ካስፈለገ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስክበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ደጀን ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ንብ/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 16 የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ መግዛት ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ብር 200,000 /ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝገቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡበት የዋጋ ማቅረቢያ ላይ የድርጅታቸውን አድራሻ በመግለጽ እና በታሽገ ፖስታ እና ማህተም በማሳረፍ ደጀን ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/በድን ቢሮ ቁጥር 18 ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ስዓት ማስገባት አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ በሎት ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማንኛውንም አሸናፊ እቃውን ገቢ በሚያደርግበት ወቅት ጥራቱን በባለሙያ ተረጋግጦ የታሸጉ እቃዎች ተፈተውና ታይተው ምንረከብ መሆኑን እንልጻለን፡፡
- ተጫራቾች አሽናፊነታቸው ከተገለጸ በኋላ የውል ማስከበሪያ አጠቃላይ ከተወዳደሩበት 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚውል ሲሆን በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ይታሸግና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታ በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙ የጨረታውን መከፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑ በተጨማሪ በጨረታው ሂደት በተላለፈ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- የጨረታው መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኃላ ተጫራቾች ካቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል እንደማይችሉ አንዲታወቅ፡፡
- ግዥ ፈፃሚው አካል ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት የጨረታ ሰነድን ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው እስከ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ሥርዝ ካለበት መፈረም አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ አሽናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃዎች ደጀን ወረዳ ፍ/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነድ ደጀን ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቢሮ ቁጥር 18 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ ደጀን/ወ/ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 18 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልከ ቁጥር 058 776 07 90 በመደወል መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡
የደጀን ወረዳ ፍ/ቤት

