ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
71

በሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር የደባርቅ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ሥር ለሚገኙት ሴክተር መስሪያ ቤቶች በመደበኛ በጀት ለ2018 ዓ.ም በጀት አገልግሎት የሚውሉ በሎት አደራጅቶ በማስቀመጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በሎት እንደሚከተለዉ ተቀምጧል፡፡ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች፣ ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች እንዲሁም  ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉት የሚገባቸው፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ከግብር አስገቢው መ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና አግባብ ያለው የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱት የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙት የዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመሂ 1 በመክፈል ደባርቅ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም (ሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ለግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ውስጥ ወይም ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም ያስያዙት (ሲፒኦ) ወይም ጥሬ ገንዘብ ከ2 በመቶ ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ ካለው በራሳቸው ፊርማ ፓራፍ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደባርቅ ዙርያ ወረዳ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  9. አሸናፊ ድረጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበሪያ 10 በመቶ (በሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ በማስያዝ ውል መያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  10. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ በጋዜጣ እትም ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡ ማለትም እስከ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም 11፡30 ድረስ ማለት ነው፡፡
  11. ይሁን እንጅ የመክፈቻ የመጨረሻ ቀን ጋዜጣው ከወጣበት በ16 ተኛው ቀን ሆኖ ይህ ቀን የበዓል (ካላንደር) ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የመንግስት የስራ ቀን ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ን/አስ አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 በግልጽ ይከፈታል፡፡
  12. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማሰፈር አለባቸው፡፡ የጨረታ ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ድምር ዋጋ ይሆናል፡፡
  13. የጨረታ መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  14. መስሪያ ቤቱ ይሄን ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. መስሪያ ቤቱ ከአሸናፊ ድርጅት ውል በሚሰጥበት ጊዜ ከጠቅላላ ዋጋው 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ አለው፡፡
  16. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈለጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስራ ሂደቱ ቢሮ ቁጥር 3 ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 058 117 04 21 ወይንም በፋክስ ቁጥር 0581170421 ደውለው መጠየቅ ይችላል፡፡

የደባርቅ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here