የድጎ-ጽዮን ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን ለኮሌጃችን አገልግሎት የሚውሉ በ2018 በጀት አመት ለሚገዙ እቃዎች ማለትም ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የህንጻ መሳሪያዎች፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስና ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት 4 ብትን ጨርቃ ጨርቅ፣ ሎት 5 የልብስ ስፌት እቃዎች እና ሎት 6 ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መጫረት የምትፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኃል፡፡
- ማንኛውም ህጋዊ የሆኑና የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የአሰሪው መስሪያ ቤትና የተጫራቹን ሙሉ ስምና አድራሻ ፊርማና ማህተም በማስቀመጥ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋን 10 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 05 የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስታና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ዋስትና የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸውን ዋናውንና ቅጁን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በድጎ-ፅዮን ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ የግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ከህዳር 29/2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም እስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ላይ ታሽጎ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ከረፋዱ 3፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ኮሌጁ 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ከላይ በሎት ከተዘረዘሩት እቃዎች ውስጥ ኮሌጁ የእቃዎችን ናሙና በሚፈልግበት ጊዜ እንዲያቀርቡ የሚጠይቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በሌላ በኩል አሸናፊው ድርጀት እቃዎችን በሙሉ በኮሌጁ ውስጥ ሊያቀርቡና በጥራት ኮሚቴው ተረጋግጦ ገቢ ይሆናል፡፡
- ኮሌጁ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ብሔራዊ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቀን ይከፈታል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 64 56 02 95 /09 13 23 29 21 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የድጎ-ጽዮን ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ

