ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
82

የወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወገራ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት እና ለወገራ ወረዳ ውሃ እና ኢነርጂ ልማት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የግንባታ እና የውሃ እቃዎችን፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የሥራ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የንግድ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለማሸነፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 ተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02  ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ ነጥብ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጽ/ቤቱ መሂ 1 በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከህዳር 29/2018 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 13/2018 ዓ/ም ለተከታታይ 15 ቀናት ይቆያል፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ታህሳስ 14/2018 ዓ/ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. የመጫረቻ ሰነዱ ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ሲሞላ ስርዝ፣ ድልዝ፣ ፍቀት እንዲታይበት አይፈቀደም፡፡ ሆኖም እንዳጋጣሚ ስርዝ፣ ድልዝና ፍቀት ቢታይበት በፊርማ/ፓራፍ/ መረጋገጥ አለበት፡፡
  12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በቀን ታህሳስ 14/2018 ዓ/ም በ4፡15 ይከፈታል፡፡
  13. የሚገዙት እቃዎች የማስረከቢያ ቦታ ወገራ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት እና ወገራ ወረዳ ውሃ ጽ/ቤት ድረስ ይሆናል፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ  ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ጨረታው የሚለየው በሎት ድምር ይሆናል፡፡
  16. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 118 05 21 ወይም ቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመገኘት ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here