ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
88

የጨረታ ቁጥር 006

የአማራ ክልል ስቴት ዩንቨርሲቲ ለ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት ለሚሰጡ መኪኖች መለዋወጫ እቃዎችን በአንድ ጊዜ በሚቀርብ ውል በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን 200,000 ( ሁለት መቶ ሺህ ) በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 (ሁለትመቶ ብር) በመክፈል በዩንቨርስቲው ግቢ ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. የሚገዙ የዕቃዎችን (አገልግሎቶችን) ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ከሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለፅ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከህዳር 29/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በዩንቨርሲቲው የግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 19 ማስገባት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ሎት በጨረታ ሰነዱ የሚገለፀውን የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በዩንቨርሲቲው ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 19 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከህዳር 29/2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም 8፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. የጨረታ ሳጥኑ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም 8፡00 ታሽጎ  8፡30 ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩንቨርሲቲው አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  11. የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  12. ዩንቨርስቲው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለዉም፡፡
  14. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 23 60 በመደወል ማግኘት ይችላሉ ፡፡

የአማራ ክልል ስቴት ዩንቨርሲቲ

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here