ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
59

የመተማ ወረዳ ፍ/ቤት እና የሁለቱ ንኡስ ወረዳ ፍ/ቤቶች የ2018 በጀት አመት እቃ አገልግሎት ግዥ ቋሚ እቃ፣ አላቂ የቢሮ እቃ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ አላቂ ጽዳት እቃ፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች እንዲሁም ህትመት (አገልግት) ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
  4. የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚያቀርቡ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱት እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ  ከማጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሰነዱን ብር 30 /ሰላሳ ብር/ ብቻ በመክፈል ገዝተው የሚወስዱ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ የቀረበውን (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነዱን ማስያዥያ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቀላላውን ነጠላ ዋጋ ድምር 2 በመቶ በማስያዝ ይህን ያላስያዘ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡ ጨረታዉ ለ15 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ይቆያል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወጥ በሆነ 2 ቅጅዎች ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 8 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከህዳር 29/2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 11፡20 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም 11:30 የጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መተማ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ/ፋ/ቢሮ ቁጥር 8 ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 በግልጽ ይከፈታል፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ጨረታው በሎት በነጠላ ስለሆነ ከሰነዱ የተዘረዘሩት በትክክል ካልሞሉ ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡
  9. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረብያ ቅጽ ላይ በተመለከተው መሰረት የእያንዳዱ እቃ (አገልግሎት) ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ መግለጽ አለባቸው፡፡
  10. በማሸጊያ ፖስታ ላይ የሚከተሉትን ነጥቦች ማስፈር ያሰፈልጋል፡፡ ማለትም ጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤት ስምና አድራሻ፣ የተጫራቾች ስም ፊርማና ሙሉ አድራሻ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን ከዋጋ ማቅረብያ ጋር አብሮ በማሸግ በጥሬ ገንዘብ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  11. አሸናፊዉ ድርጅት ያሸነፈዉን እቃ መተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቢሮ ቁጥር 8 ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  1. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በሞባይል ቁጥር 09 18 43 22 26 በመደወል ወይም መተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የመተማ ወረዳ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here