በደቡብ ወሎ አስተዳደር ዞን የተንታ ወረዳ ፍ/ቤት የ2018 በጀት አመት ለቢሮ አገልግሎት የሚዉሉ እቃዎችን ሎት 1 የደንብ ልብስ፣ ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 3 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 4 ልዩ ልዩ ህትመት፣ ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 6 ተሰርተዉ የሚሸጡ ፈርኒቸር ወይም (ቋሚ) እቃዎች እንዲሁም ሎት 7 የሚሰሩ ቋሚ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት (ለማሰራት) ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታዉ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ከላይ በተጠቀሱት የአቅርቦት ዘርፎች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የግብር ክፍያ መለያ ወይም (ቲን) ያላችሁን ማስረጃዎቹን ማቅረብ የምትችሉ፡፡
- የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ አሴት ታክስ ወይም (ቫት) ከፋይነትን የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከ1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ከተንታ ወረዳ ፍ/ቤት ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 6 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሎት የማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ ብር/ ከፍለዉ ከተንታ ወረዳ ፍ/ቤት ከዋና ገንዘብ ያዥ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት እቃ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ወይም የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በስማቸው የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች ያሸነፈዉን ዋጋ በተናጠልም ሆነ በጥቅል ዋጋ ከብር 10,000 /አስር ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ ሶስት በመቶ የሚከፍል ይሆናል ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛዉ ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተንታ ወረዳ ፍ/ቤት ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በተንታ ወረዳ ፍ/ቤት ዉስጥ ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16 ተኛዉ ቀን 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ ቀን 4፡00 ተዘግቶ በዚያዉ ቀን 4፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊ መሆን የሚቻለዉ የተጫረቱበት ዘርፍ በሎት ዝቅተኛ ዋጋ የሰጡ መሆኑን ታዉቆ ለሞሉት ጥቅል እቃዎች ዋጋ ማስያዝ ሲችሉ ነው ፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉትን አቅርቦት ከተንታ ወረዳ ፍ/ቤት ን/ክፍል ድረስ በራሳቸዉ ወጭ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀን ዉል መፈጸምና የዉሉን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ ማስያዝ አለበት፡፡
- ሌሎች ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሁነዉ የእቃዉን ብዛት እስከ 20 በመቶ የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በዓል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለዉ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ሰዓት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- አቅራቢዉ በዉሉ መሰረት በጊዜዉ አጠናቆ ባያቀርብ በዉሉ የተመለከተዉን ገንዘብ መጠን ላይ በየቀኑ አንድ በመቶ መቀጫ እንደሚከፍል ማወቅ አለበት፡፡
- ተጫራቾች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይቻልም፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መግለጫ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 441 02 61 ወይም 09 06 91 64 97 በመደወል መረጃ ማገኘት ይችላሉ፡፡
የተንታ ወረዳ ፍርድ ቤት

