የወግዲ ወረዳ ፍ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የጽሀፈት መሳሪያዎች ሎት1. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት2. ቋሚ አቃዎች፣ ሎት3. የህትመት ውጤቶች ፣ሎት4. የህንጻ ቁሳቁስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ለያንዳንዱ የንግድ ዘረፍ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት የማይመለስ 50 (ሀምሳ ብር) በመክፈል ወግዲ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ የስራ ሂደት ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም (ቢን ቦንድ) የሚወዳደሩበት የንግድ ዘርፍ የዕቃዉን ጠቀላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሰቡን (ሰነዱን) አንድ ወጥ በሆነና በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ወግዲ ወረዳ ፍ/ቤት የግ/ን/አስ/ድን በተዘጋጀዉ የጨረታ ሰነዱን ዉስጥ በጋዜጣ ካወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ታትሞ ይቆይና በ16 ኛዉ ቀን 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ላይ ይከፈታል ፡፡ የሚከፈትበት ቀን የበአል ቀን ከሆነ የሚቀጥለዉ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታዉን በሎት ጠቅላላ ድምር የሚያወዳድር ሲሆን ከተዘረዘሩት ዕቃዎች ዉስጥ ሳይሞሉ መተዉ አይቻልም፡፡ ማንኛዉም ተጫራች የሚወዳደርበትን ሎት ውስጥ ሁሉንም ካልሞላ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀ ከ15 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ያሸነፈዉን ዕቃ ጠቀላላ ዋጋ 10በመቶ (አስር በመቶ) የዉለታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት እቃዉን የሚያስረከበዉ በወግዲ ወረዳ ፍ/ቤት ንብረት ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 ነዉ፡፡
- የሚሞላዉ ዋጋ ማንኛዉም ግብር የከፈለ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆነ ቫቱን ጨምራችሁ መሙላት አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾች በፖስታ ላይ የጨረታዉን ቁጥር ፤ የሚጫረቱበትን የንግድ ዘርፍ ፣ ፊርማ ፣ ማህተም ፣ ቀን መጻፍ አለባችሁ፡፡
- በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈለጉ ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ወግዲ ወረዳ ፍ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 14 06 85 76 ወይም 09 14 33 85 16 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ፍ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ መ/ቤቱ ያወጣዉን ሰርዞ የራሱን እስፔስፍኬሸን መፃፍ የለበትም ይህን ካደረጉ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡
የወግዲ ወረዳ ፍ/ቤት

