የምዕራብ ጎጃም ዞንና አካባቢው አማራ ልማት ማህበር ማ/ጽ/ቤት master cared foundation UNICEF ከተባለ ግበረ-ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በፍ/ሰላምና ዳንግላ ከተሞች በብቁ ወጣት ፕሮግራም ዘርፍ በሥራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ ሥራዎችን እየሰራን እንገኛለን፡፡ ለዚህ ተግባር ግብዓት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግዥዎች ማለትም የዶሮ እርባታ ግብዓት ቁሳቁስ፣ የእንቁላል ዶሮ፣ ፈርኒቸር፣ ዴስክቶፕ ኮምፒውተር እና ፕሪንተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (ቲን)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያያዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ምዕ/ጎ/ዞን አልማ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚወዳደሩበትን የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (በጥሬ ገንዘብ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች መሰረት በማድረግ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በምዕ/ጎ/ዞን አማራ ልማት ማህበር /አልማ/ ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በዚሁ በ7 ተኛው ቀን ከቀኑ 11:30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በ8 ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ለሚሰራው ሥራ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ (ሲፒኦ) ካስያዘ በኋላ በውሉ ላይ በተጠቀሰው የሥራ ቀናት ውስጥ ዕቃዎችን ፍ/ሰላምና ዳንግላ ከተሞች ድረስ በመከፋፈል ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የዕቃውን ዝርዝር (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ጋር ማግኝት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ አሸናፊው እንደአስፈላጊነቱ በነጠላ ወይም በድምር ዋጋ የሚለይ ይሆናል፡፡
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የምዕ/ጎ/ዞን አማራ ልማት ማህበር ማ/ጽ/ቤት

