ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
79

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የባንጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣ ሎት 2 ቋሚ እቃ ጀነሬተር፣ ሎት 3 የመኪና ጎማ ከነካላማዳሪው፣ ሎት 4 የጽዳት እቃ እንዲሁም ሎት 5 ሌሎች አላቂ እቃዎች ከመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ የዋጋውን ጠቅላላ 10 በመቶ ማስያዝ የሚችል፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተወዳዳሪዎች የንግድ ፈቃዳቸው በሚጋብዛቸው ብቻ መወዳደር አለባቸው፡፡
  7. የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ባንጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ በድን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ለመኪና ጎማ ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ለኤሌክትሮኒክስ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ለጀነሬተር ብር 8,000 /ስምንት ሺህ ብር/ ለሎት 4 የጽዳት እቃ ብር 2,000 /ሁለት ሺህ ብር/ ለሎት 6 ሌሎች አላቂዎች ብር 2,000 /ሁለት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ደረሰኝ በመሂ 1 ኮፒ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም፡፡
  10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ፖስታ በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በባንጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16 ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ጨረታው ከወጣበት በ16 ተኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይታሸጋል፡፡ በዚህ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
  12. አሸናፊ የምንለየው ጥራቱን የጠበቀ እቃ ካቀረቡት ውስጥ በየሎቱ በጠቅላላ ድምር በዝቅተኛ ዋጋ የሞላውን ነው፡፡
  13. አሽናፊ ድርጅት ያሸነፏቸውን እቃዎች ባንጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በባለሙያ እያስፈተሽ ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ወጭ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
  14. ስለጨረታ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ባንጃ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ግ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 227 06 47 /058 227 00 09/ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  15. የባንጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት እንደ ሴክተር መ/ቤቶች በጀት አቅም 20 በመቶ የመጨመር እና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  17. የጨረታ ሳጥን የሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት በተመሳሳይ ቦታና ስዓት የይከፈታል፡፡

የባንጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here