የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ መሥሪያ ቤቶች በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የስፖርት ትጥቅ፣ ሎት 3 የጽዳት እቃ፣ ሎት 4 ፈርኒቸር፣ ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ እንዲሁም ሎት 6 የቢሮ መገልገያ እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከህዳር 29/2018 እስከ ታህሳስ 30/2018 ዓ.ም የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 31 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የድምር ሎት 1 ብር 40,00፣ ሎት 2 ብር 8,000፣ ሎት 3 ብር 5,000፣ ሎት 4 ብር 7,500፣ ሎት 5 ብር 60,000 እና ሎት 6 ብር4,500 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከዋና ገንዘብ ያዥ በደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በ2 ኮፒ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) ኦርጅናል ሰነዱ ውስጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 35 የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ታህሳስ 14/2010 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ቢኖሩም ባይኖሩም ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 35 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 117 00 86 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መስሪያ ቤቱ የጨረታ ውበቱን ጠቅላላ ድምር ውጤቱ ያያል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ንብረቱን ደባርቅ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 34 ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ሙሉ ስማቸውን ፊርማቸውን እና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
የደባርቅ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት

