በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የፖሊስ ዋ/ጠ/መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ሎት 1 የሰራዊት ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዝቅተኛ ዋጋ ካቀረበዉ ድርጅት መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የሚነበቡ (በደንብ የሚታይ) ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጥቃቅን እና አነስተኛ የሚወዳደሩ የንግድ ፈቃዳቸው አምስት ዓመት ያልሞላው ለመሆኑ ከቴክኒክና ሙያ ጽ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ አለባችው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ላይ የሚገለጸውን ዋጋ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 13 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን ቴክኒካልና ፋይናንሺያል በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ ፖሊስ ዋ/ጠ/መምሪያ በግዥና ፋይናንስ መምሪያ ወይም ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚውል ሲሆን በ16 ተኛው ቀን ጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ በእለቱ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 21 11 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 14 53 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ

