ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
8

የላይ ጋይንት ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን  ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እንዲሁም ሎት 3. የፈርኒቸር እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅት ወይም ተጫራች መጫረት ይችላል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ጨረታው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የሚገዙ የእቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኝት ይችላሉ፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱ መሸጫ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመያዝ መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም (ቢድ ቦንድ) በሚወዳሩበት ብር የሚመለስ 2 በመቶ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ ወይም (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግዥ እና ፋይናንስ ንብረት አስተዳዳር ደጋፊ የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 18 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ለ15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን በዚህ ቀን 11፡30 በኋላ የጨረታ ስጥኑ ይታሸጋል፡፡
  10. በ15ኛው ቀን ውስጥ በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሰራ ሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 18 ከጠዋቱ 3፡00 ይከፈታል፡፡
  12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 18 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በመላክ በስልክ ቁጥር 058 445 13 65 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የላይ ጋይንት ወረዳ ፍ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here