ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
11

ጣና ኮሙኒኬሽን ኃላፊነት የተወሰነ የግል ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ያገለገሉ ሊፋን መኪናዎች እና ታታ ሲንግል ፒካፕ መኪና በሀገር ዉስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ 1. ሞዴል 520 ያገለገለ ሊፋን መኪና 2. ታታ ሲግል ፒካፕ መኪና ኩባንያዉ ከ1-2 የተገለጹትን ያገለገሉ ሊፋን እና ታታ ሲንግል ፒካፕ መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ቀናት ይውላል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ ድርጅቶች በጨረታዉ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች ለሚገዟቸዉ መኪኖች ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸዉ እና የግብር ከፋይ ማስረጃ (ቲን) ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  2. ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁትን ተሽከርካሪ መኪኖች በቦታዉ ድረስ በመምጣት በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00-10፡00 ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቱን በአካል ማየት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ እና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) እየከፈሉ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 11 ከአሽርፍ 300 ሜትር ገባ ብሎ ጣና ኮሙኒኬሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር (ጣና ሞባይል ፋብሪካ) በመምጣት መረጃ በመጠየቅ ለ10 ተከታታይ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ኩባንያዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 18 35 38 34 ወይም 09 18 35 36 38 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ጣና ኮሙኒኬሽን ኃላፊነት የተወሰነ የግል ማህበር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here