የጃ/ጠ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግ/ንብ/አስ/ቡድን በበጀት አመቱ ለጃ/ጠ/ወ ሴክተር መ/ቤቶች የተፈቀደውን በጀት መሠረት በማድረግ ሎት 1. አላቂ የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. የጽዳት እቃ፣ ሎት 3. ኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ ሎት 4. የውሃ እቃ፣ ሎት 5. የስፖርት አልባሳት እንዲሁም ሎት 6. የሙዚቃ መሳሪያ ሲሆኑ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ወይም ማስቀረብ ይፈልጋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚባሉት ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ ሆናቸውን የሚያረጋገጥ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን ህጋዊ መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ የፁሁፍ ማመልከቻ በማቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምር በጃ/ጠ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ድረስ በመቅረብ በእያንዳንዱ ሎት የሚደመስስ ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የሚጫረቷቸው እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ አንድ በመቶ በገቢ ደረሰኝ ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) በጽ/ቤቱ ስም ማስያዝ አለባቸው ወይም (የቫት) ተመዝጋቢዎች ከሆኑ የሚሞሉት ጠ/ድምር ቫትን ጨምር ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታ አሸናፊ ከሆነ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ የሚቆጠር በተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡ ዕለቱ ህዝባዊ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ (የመወዳዳሪያ) ፖስታቸውን በጥንቃቄ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ስማቸውን አድራሻቸውንና የድርጅቱ ስም፣ ማህተም፣ ፊርማ በማድረግ ማስገባት አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በውሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው በሎት ስለሚታይ ተጫራቾች የተገለጹትን የዕቃ ዝርዝሮች ሙሉ በሙሉ ካልሞሉ ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ የሚያስረክቡበት ጃ/ጠ/ወ/ሴክተር መ/ቤቶች ባሉ ንብረት ከፍሎች መሆኑን እናሳውቃስን፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ያልተገለፁ ሁኔታዎች ቢኖሩ 2003 ዓ.ም በወጣው የገዥ መመሪያ ተገዥ መሆን አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ ከሚገዛው እቃ ላይ 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላሉ፡፡
- ስለጨረታው ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 01 በአካል በምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 775 20 61 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጃ/ጠ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት

