ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
30

የምእራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለምእ/ጐ/ም ዞን መምሪያዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን ሎት1. የጽ/ መሳሪያ፣ ሎት2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት3. የፕሪንተርና የፎቶ ኮፒ ቀለሞች፣ ሎት4. የውጭ ሀገር ፈርኒቸር፣ ሎት5. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት6. የቀላል መኪኖች ጐማ፣ ሎት7.የኤሌክትሪክ መሳሪያዎች እና ተዛማጅ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ ህጋዊ አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት)ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ከዚህ ጋር በተያያዘ የዋጋ መሙያ መሰረት ዋጋ በመሙሉት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው በቀረበው ዝርዝር መሠረት በጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ድርጅት ሲሆን በጥቅል ድምር አሸናፊ የሚለይባቸው እቃዎች ለአንድም ዕቃ አለመሙላት ከጨረታ ውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) የሚሸጥ ሲሆን ሰነዱ ከተቋማችን ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ዕቃ ጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ለምዕራብ ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ምዕ/ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ማስታወቂያው በጋዜጣ  ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በምእ/ጐ ዞን ገን/መምሪያ በ3፡30 ታሽጐ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ እለቱ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን  በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል፡፡
  11. የጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒዩ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ማስያዝ እና አቃዎችን ምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ንብረት ክፍል ድረስ የማጓጓዣ  ወጭውን ችሎ ማስረከብ አለበት፡፡
  12. መስሪያ ቤቱ 20በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡ የተሻለ ዘዴ ካገኘም ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በማስታወቂያው ላይ ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ ፡፡
  14. ተጫራቾች የዕቃዎችን ናሙና ምዕራብ ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ቢ/ቁ 26 ቀርበው ማየት ይችላሉ፡
  15. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 05 87 75 08 95 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

የምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here