ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
84

የሰሜን ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ በዞኑ አስተዳደር ስር ላሉ መምሪያዎች አገልግሎት የሚዉሉ የእስቴሽነሪ፣ የጽዳት እቃ፣ የመኪና ኢንሹራንስ እና ሶስተኛ ወገን እንዲሁም የቦርሳ እቃዎች በግልጽ ጨረታ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጫረታ ሰነዱን ከሰሜን ጎጃም ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 08 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጨረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ አገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት አምስት የስራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈረም አለበት። በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል ካልፈፀመ ቢሮው ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያ በመውረስ የራሱን አማራጭ ይወስዳል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ብር ለእስቴሽነሪ 50,000 ብር ፣(ሃምሳ ሽህ ብር) ፣ ለጽዳት እቃ 25,000 ብር (ሃያ አምስት ሽህ ብር) ፣ የመኪና ኢንሹራስ እና ሶስተኛ ጋን 50,000 ብር (ሃምሳ ሽህ ብር) እና የቦርሳ 10,000 ብር (አስር ሽህ ብር) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  9. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (ለአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ይዘጋና በዚሁ ቀን በ4፡30 የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰሜን ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት 16ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡ በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በቢሮው የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴዎች ጨረታው ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ሰሜን ጎጃም ዞን ገንዘብ መምረያ ቢሮ ቁጥር 11 መቀመጫዉን በባህርዳር ኩተማ ቀበሌ 16 የተባበሩት ማደያ ጀርባ የአማራ ህንጻ ዲዛይን ከተከራየዉ ቢሮ ለዚህ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የመጫረቻ ሰነዱ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውጭ ዘግይቶ ለቢሮአችን ቢደርስ የጨረታ ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  11. በጨረታው አሸናፊ የሆኑት ድርጅቶች ሁሉንም ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች በተጠየቀው ዝርዝር መግለጫ መሰረት ማቅረብ አለባቸው’፡፡
  12. በተጨማሪ በግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 እና ተሻሽሎ በቀረበው የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።

የሰሜን ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here