ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
75

የአገው ግ/ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን ማለትም ህትመት፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እስቴሽነሪ እና የመኪና ጎማ የመሳሰሉትን ግብዓቶች በግልፅ ጨረታ በሎት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ( ሠርቲፊኬት) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥ መጠን ከ200,000.00 (ከሁለት መቶ ሺ ) ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባችዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ በተቁ 1-3 የተጠቀሱትንና ማስረጃዎችን ማለትም የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ቲን፣ ሰርተፍኬትና የቫት ሰርተፍኬት የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ፖስታ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጋዜጣ  ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ  11፡30 ድረስ በስራ ስዓት የጨረታ ሰነዱን አገዉ ግ/ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግዥ ፋ/ን/አስ/ር/ደ/ የሥራ ሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 46 የማይመለስ ብር 00  (አንድ መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. የሁሉም የእቃ ዓይነቶች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ድምር በሎት በተቀመጠው መሠረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በሆስፒታሉ የገቢ ደረሰኝ /መሂ-1/ ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ ፖስታ በማሸግ አገዉ ግ/ቤት

የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግዥ ፋ/ን/አስ/ር/ደ/የሥራ ሃደት ቢሮ ቁጥር 46

በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከ06/04/2018 ዓ/ም ለተከታታይ 16 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሳጥኑ ከሚታሸግበት የመጨረሻ ሰዓት እና ደቂቃ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አገዉ ግ/ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግዥ ፋ/ን/አስር/ደ/የሥራ ሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 46 በ16ኛው ቀን የጨረታ ሣጥነ የሚከፈተዉ ከጥዋቱ 4፡00 ታሽጐ ከጥዋቱ 4፡15  ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ ነገር ግን በ16ኛው ቀን  ብሔራዊ በዓል ወይም እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ታሽጐ ከጥዋቱ  4፡15 ይከፈታል፤ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ካልተገኙ የጨረታ ሰነዱ እንዲከፈት ተደርጎ ያልተገኙ ተጫራቾች ግን በእለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ   ይሆናሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ንግድ ፈቃዳቸው በሚጋብዛቸው ብቻ መወዳደር ይችላሉ ይሁን እንጅየሚሞላዉ ዋጋ ማንኛዉንም የመንግስት ግብር፣ የትራንስፖርት ወጭና ሌሎች ወጭዎች ካሉ ማካተት ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ያአሸነፉትን እቃዎች አገዉ ግ/ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ በራሳቸው ወጭ በማምጣትና በባለሙያ እና በጥራት አረጋጋጭ ኮሚቴ በማስፈተሽ ወይም በማስመርመር የማስረከብ ግዴታ አለባቸዉ፡፡
  4. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሰው መጫረት የተከለከለ ነው፡፡
  5. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ  የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  6. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 22 40 531 /058 22 40 532 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአገዉ ግ/ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

 

 

 

 

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here