ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
69

በምሥራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን የእነማይ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በሥሩ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን ከመደበኛ በጀት እና ከመደበኛ ካፒታል በጀት ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች፣ ሎት 2. ኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት 3. የኮንስትራክሽን ማቴሪያል እቃዎች፣ ሎት 4. የውጭ ሀገር ፈርኒቸር፣ ሎት 5. የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት 6 የጽዳት እቃዎች ሎት 7. የመኪና ጎማ ከእነካለመንዳሪው፣ ሎት 8. የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 9. የህትመት ሥራዎች እንዲሁም ሎት 10. የወጥ ቤት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ዝርዝር መረጃውም በጨረታ ሰነዱ ተካቷል፡፡ በጨረታው ለመሣተፍ መሟላት የሚገባቸው፡-

  1. በዘርፉ አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ግዥው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ 3 በመቶ ታክስ የሚቆረጥ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ አለባቸው፣ የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዝጋቢ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ለእያንዳንዱ ሎቶች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ከሎት 1 እስከ ሎት 5 ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ ከሎት 6 እስከ ሉት 10 ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እነማይ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የፋይናንስ ቡድን ከገንዘብ ያዥ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ማለትም ከሎት 1 አስከ ሎት 3 ብር 50,000 (ሃምሳ ሽህ ብር) ብቻ ሎት 4፣5 ፣7 እና ሎት 8 ብር 10,000 (አስር ሽህ ብር) ብቻ ሎት 6፣9 እና 10 ብር 5,000 (አምስት ሽህ ብር ) ብቻ በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ከሆነ ገንዘቡን በመ/ቤታችን መሂ 1 ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
  5. ከሎት 1 እስከ ሎት 10 ላሉ ግዥዎች አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ቀን በኋላ ለውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለበት፡፡
  6. ከሎት 1-10 አሸናፊ ድርጅት ውል በሚይዝበት ወቅት እ/ወ/ዐቃቢ ህግ የሚያስከፍለውን የአገልግሎት ክፍያ ሙሉ ወጭ መሸፈን አለበት፡፡
  7. ለሎት 3 የኮንስትራክሽን ማቴሪያል እቃዎች ከጨረታ ሰነዱ ላይ በማየት የአባይ አሸዋ በየቀበሌው የሚራገፍ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡
  8. ለሁሉም ሎቶች ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት ቆይቶ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ይታሸግና በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉልም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እሁድ እና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ታሽጎ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡ በጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ወይም ለመለየት አሻሚ የሆነ ነገር መኖር የለበትም ካለም ተጫራቹ ፖራፍ ማድረግ አለበት፡፡ በጨረታ ሰነዱ እና በፖስታው ላይ የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡
  9. በባለሙያ የሚረጋገጡ እቃዎችን በባለሙያ እየተረጋገጡ የምንረከብ መሆኑ እና አሸናፊው ተጫራች የአሽነፈባቸውን እቃዎች በእነማይ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ሥር ባሉ ንብረት ክፍል ድረስ አስፈላጊውን ወጭ በመሸፈን ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
  10. በእያንዳንዱ ሎት መስሪያ ቤቱ አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ዋጋ ጥቅል ድምር ዝቅትኛ ዋጋ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ተጫራቾች በየሎት ምድቡ የቀረቡትን ሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው፡፡ ዝርዝሩን ሙሉ በሙሉ ካልሞሉ ከጨረታ ውጭ ውድቅ ይሆናሉ፡፡
  11. ከሎት 1-10 ላሉ የሎት ምድቦች ጽ/ቤቱ የጨረታ አሸናፊ ከሆነው ተጫራች የጨረታ ይዘት ሣይቀይር ከእቃው ከጠቅላላ መጠን ላይ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  12. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ አስፈላጊ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  13. የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች በአቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 665 01 00 /058 665 00 08 ደውሎ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የእነማይ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here