በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የዳንግላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት አመት ለሴ/መቤቶች የተለያዩ ሎት 1 እስቴሽነሪ፣ ሎት 2 የግንባታ ዕቃዎች፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 4 አሽዋ፣ ሎት 5 ኢምፖርትድ ፈርኒቸር፣ ሎት 6 የመኪና ጐማ፣ ሎት 7 የቢሮ መጋረጃ ከነአክሰሰሪው በሙሉ፣ ሎት 8. የኮፒውተር ቀለም፣ ሎት 9. የጽዳት እቃ እንዲሁም ሎት 10. ቋሚ አላቂ እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለሚገዙ እቃዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ለማወዳደር ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን በሎት ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚሸጡ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ከሎት 1 እስከ 8 ብር 10,000 (አስር ሽህ ብር) ሲሆን ሎት 9 እና 10 ብር 3,000 (ሶስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመሂ 1 ከሆነ በገ/ያዦች አስይዞ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ን/አስ/ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 4 የማይመለስ ብር ከሎት 1 እስከ ሎት 9 እያንዳንዳቸው ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቄያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሣቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ በዳንግላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ/ን/አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 16ኛው ቀን በስራ ሰዓት ከረፋዱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በእለቱ ከረፋዱ 4፡00 ላይ ይታሸጋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የግዥን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 በ16ኛው ቀን 4፡15 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ስዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ መ/ቤቱ ያወጣውን ጨረታ እንደ ወረዳው በጀት 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ከላይ ከተጠቀሱት ነጥቦች በተጨማሪ በክልሉ የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2003 ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 140 06 82 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡ አሸናፊው የሚለየው በየሎቱ በድምር ዋጋ በማወዳደር ነው፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ በዳንግላ ወረዳ /ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ሥር በሚገኙ በ6ቱ ንብረት ክፍሎች በሚሰጠው ዝርዝር መሰረት ተዘዋውሮ በማስረከብ በራሳቸው ወጭ በማምጣትና በጥራት አረጋጋጭ ኮሚቴ በማስፈተሽ (በማስመርመር) የማስረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በቀረቡት የሎቱ ዝርዝሮችን ውስጥ በሙሉ ዋጋ መሙላት ግዴታ ነው፡፡ ካልሞላ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
የዳንግላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

