ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
77

በምሥራቅ ጎጃም ዞን በክላስተር ደረጃ ለአራቱ ወረዳዎች ማለትም የጎ/ ወረዳ ፍ/ቤት፣ የአዋባል ወረዳ ፍ/ቤት፣ የባሶሊበን ወረዳ ፍ/ቤት የአነደድ ወረዳ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ለ2018 በጀት ዓመት ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. ኮምፒዉተር እና ተዛማጆች እቃዎች፣ ሎት 3. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 4. የህትመት  ውጤቶች፣  ሎት 5. ኤሌክትሪክና ተዛማጅ እቃዎችን፣ ሎት 6.  የህንጻ መሳሪያዎች፣  ሎት 7. የዉጭ ፈርኒቸር፣ ሎት 8. ፎቶ ኮፒ ማሽንና ኮምፒዉተርና ተዛማጅ እቃዎች ጥገና እንዲሁም  ሎት 9. የካዝና ጥገና ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. በ2018 ዓ/ም በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃዎች ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግዥ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም (ቫት) ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ኮምፒዉተርና ተዛማጅ እቃዎች ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በታችም ጠቅላላ ዋጋ ቢሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት አብሮ ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳታፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ለሚገዙት እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ  ብር 20 (ሃያ ብር) በመክፈል ከሎት 1 እስከ ሎት 9 ድረስ የጨረታ ሰነዱን የ4ቱንም  ወረዳ ፍ/ቤቶች ከጎዛምን ወረዳ ፍ/ቤት  ገንዘብ ያዥ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩት አንድ በመቶ ከ1-9 ላሉት ሎቶች  በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት 11፡00 ድረስ ዘወትር በሥራ ስዓት  ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማደረግ የጎ/ወ/ፍ/ቤት፣ የአዋባል ወ/ፍ/ቤት፣ የባሶሊበን ወ/ፍ/ቤት የአነደድ ወ/ፍ/ቤት የሁሉንም ወረዳዎች ጎዛምን ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ለእያንዳንዱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16 ተኛው ቀን እስከ 2፡59 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 3፡00 ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች በተገኙበት ይታሸጋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የ4ቱም ወረዳዎች ጎዛምን ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ በ16 ተኛው ቀን 3፡30 ጀምሮ የሚከፈት ሲሆን ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ፖስታው መከፈቱ የማይስተጓጎል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  10. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በዓል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
  11. የጨረታ አሸናፊ መሆን የሚቻለው በሎት በጥቅል ዋጋ ዝቅተኛ ያቀረበ ተጫራች መሆኑ ታውቆ የሁሉም እቃዎች ዋጋ መሙላት ይኖርበታል፡፡ እና በዋጋ በመሙያዉ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ስም፣ ፊርማ እና ማህተም መደረግ ይኖርበታል፡፡
  12. መ/ቤቱ ከተዘረዘረው ግዥ መጠን 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  13. አሸናፊው ከጠቅላላ ዋጋው ውስጥ 10 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (በሲፒኦ) ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  14. አሸናፊው ድርጅት እቃውን  በራሱ ትራንስፖርት፣ የአዋባል ወ/ፍ/ቤት፣ የባሶሊበን ወ/ፍ/ቤት የአነደድ  ወ/ፍ/ቤት ጎዛምን ወረዳ ፍ/ቤት  ባሉበት ወረዳ   አጓጉዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጣው ወጭ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፡፡
  17. የመጫረቻ ሰነድ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
  18. አሸናፊዉ ድርጅት በስማቸዉ የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለዉ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  19. ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር የጎ/ወ/ፍ/ቤት 058 771 31 29 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአነደድ ወረዳ ፍርደ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here