ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
70

የወጀት ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የገልባጭ መኪና በግልጽ ጨረታ ግዥ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ  ህጋዊ  የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100 ብር (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. የተሞላው ዋጋ ማንኛውንም ግብር ወይም ታክስ ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያና ዋስትና ለሚወዳድሩበት ብር ወይም ዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲ.ፒ.ኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች የዋጋ መሙያ ሰነዳቸዉ ላይ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በፖስታ በማሸግ ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
  10. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ጨረታው ከወጣበት ቀን ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት  ታትሞ ይቆይና በ11ኛው ቀን በ3፡30 ተጫራቾች  ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙ ይከፈታል፣ ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት አያስተጓጉልም፡፡
  11. የእቃዉን ማጓጓዣ ወጭ የጨረታ አሸናፊዉ ይሸፍናል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 13 75 77 87 /058 325 62 53 / 09 10 88 97 28 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  14. ስለ ጨረታው ያልተገለጹ ነገሮች ቢኖሩ በ2003 የግዥ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

የወጀት ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here