ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
81

የአብናት ወረዳ ፖ/ቴ/ኮሌጅ ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት ለትምህርት ስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 2. ICT ሎት 3.  ኮንስትራክሽን፣ ሎት 4. የብረታ ብረት ሎት 5. የፈርኒቸር፣ ሎት 6. የእንስሳት ጤና፣ ሎት 7. የጋርመነት (የልብስ ስፌት ማሰልጠኛ)፣ ሎት 8.የጽህፈት መሳሪያና የጽዳት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መወዳደር ለምትፈልጉ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡

  1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ ሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስከር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. በማንኛውም ግዥ ለዕቃዎች ከብር 20,000 (ሃያ ሽህ ብር) በላይ ለአገልግሎት ግዥ ከብር 10,000 (አስር ሽህ ብር) እና በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢው ከሚፈፀምለት ከፍያ ላይ 3 በመቶ ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፡፡
  8. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ እና ፖስታው ላይ የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ መሆን የለበትም ከሆነም ፓራፍ ያድርጉ፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማያያዝ አለባቸው፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ በሁለት ፖስታ ግ/ፋ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር የሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባችዋል፡፡
  12. ኮሌጁ የሚገዛውቸን እቃዎች 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
  13. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የቀረቡትን እቃዎች ሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው አንድም እቃ አለመሙላት ከውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
  14. የጨረታውን አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኝት ይችላሉ፡፡
  15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 መግዛት ይችላል፡፡
  16. የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ጨረታው ለተጫራቾች ከፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች እስከ 15 ተኛው ቀን ዘወትር 2፡30 እስከ 6፡30 እና ከሰዓት 7፡30 እስከ 11፡30 ባለው ጊዜ ለጨረታ የቀረበውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  17. ኮሌጁ አሸናፊውን በጥቅል ዋጋ ይመርጣል (ይለያል)፡፡
  18. ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በ16ኛው ቀን ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ በሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
  19. አሸናፊው ድርጅት የአሸነፋቸውን እቃዎች እብናት ወረዳ ፖሊ ቴ/ኮሌጅ ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ አለበት፡፡
  20. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  21. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ የጨረታ አሸናፊውን የውል ማስከበሪያ የውል ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) በማስያዝ ውል መውሰድ አለባቸው፡፡
  22. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህግና ደንቦች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡
  23. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 446 08 58 /09 28 66 75 96 /09 18 18 81 28 ደውለው ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአብናት ወረዳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here