ግልጽ  የጨረታ  ማስታወቂያ

0
66

የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት የመኪና ጎማ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና በሙያዉ የተሰማሩ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የሚሳተፉ ተጫራቾች የእቃ (የአገልግሎቱን) ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የሚገዙ እቃወች (አገልግሎቶች) አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 33 የጨረታ ሰነዱን ማግኘትና ማየት ይቻላል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ ) በመክፈል 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 33 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚፈልጉ ለጽ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመክፈል ደረሰኙን ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክተር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 በተዘጋጀው ቀን የጨረታ ሣጥን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ወይም  ህጋዊ  ወኪሎቻቸው  በተገኙበት  በግዥ  ፋይ/ንብ/  አስተዳደር  ዳይሬክቶሬት  የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ በእለቱ ወይም በቀኑ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ
    ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጽ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው።
  9. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 30 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 220 1068 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 2030 በመደወል ማግኘት ይቻላል።

የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here