ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
83

በሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኘው ለጃናሞራ ወረዳ ስራና ስልጠና ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በመ/ብርሃን ቀበሌ 01 ሸድ ግንባታ በሙሉ ዋጋ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የህንጻ ግንባታ ሥራ ተቋራጭ የታደሰና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  2. ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ በህንጻ ግንባታ ስራ ተቋራጭ የታደሰ ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. ለተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ማረጋገጫቸውን ሰርተፊኬት ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የግንባታው አይነትና ዝርዝር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና5 በመቶ ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ማለትም በአማረኛ የተተረጎመ (ሲፒኦ) ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመሂ 1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ቀናት ከታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ዓ.ም እስከ ህዳር 26/04/2018 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 10 በቀን ታህሳስ 27/2018 ዓ/ም 8፡15 ታሽጎ 8፡30 በይፋ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኝም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል ፡፡
  10. ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር ሲሆን ጨረታው ለ40 ተከታታይ ቀናት ፅንቶ ይቆያል፡፡
  11. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለው ውድቅ ይደረጋል፡፡
  12. ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 294 00 23 /24 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here