ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
113

በአብክመ ለእብናት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የደንብ ልብስ፣ ሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 5 የቤትና የቢሮ እቃዎች እና ሎት 6 ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መወዳደር ለምትፈልጉ የመወዳደሪያ መስፈርቱ እንደሚከተለው ተቀምጧል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
  4. ግዥው 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  5. በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል በእ/የመ/ደ/ሆ/ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ሁለት በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናሉን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርጎ እ/መ/ደ/ሆ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  8. ሆስፒታሉ የሚገዛቸውን እቃዎች ሃያ በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
  9. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የቀረቡትን እቃዎች ሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው አንድም እቃ አለመሙላት ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
  10. የሚገዙትን እቃዎች አይነት ስፔስፊኬሽን/ መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  11. ጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡
  12. ሆስፒታሉ አሸናፊውን በጥቅል ዋጋ ይመርጣል፡፡
  13. ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በ16ኛው ቀን ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም የህዝብ በዓል ከሆነ በቀጣዩ በሥራ ቀን ከቀኑ 8፡oo ታሽጎ በ8፡30 ይከፈታል፡፡
  14. አሸናፊው ድርጅት የአሸነፋቸውን እቃዎች ለእብናት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ የሚችል፡፡
  15. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ተጫራቾች በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ስትሞሉ ሥርዝ ድልዝ (በፍሉድ) የጠፋ መኖር የለበትም፡፡
  17. አሸናፊው ተጫራች በስሙ የታተመ ህጋዊ ደረሰኝ ያለው መሆን አለበት፡፡
  18. ደረቅ ቸክ ማስያዝ አይቻልም፡፡
  19. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን አስር በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ በማስያዝ ውል መውሰድ አለባቸው፡፡
  20. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  21. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ30 ቀን ይሆናል፡፡
  22. በተለያየ ምክንያት የጨረታ ሰነዱ ችግር ቢኖርበት ይህ ማሰታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስተካከያ የሚደረግበት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  23. ተጫራቾች ለማሸነፍ ሲባል የተወሰኑትን እቃዎች በጣም በዝቅተኛ ዋጋ ሞልቶ አላቀርብም /ገቢያ/ ላይ የለም ማለት አይቻልም፡፡
  24. በዚህ ሰነድ ላይ ያልተገለፀ ሀሳብ ቢኖር በግዥ መመሪያው መሰረት ተግባራዊ ይሆናል፡፡
  25. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በሥልክ ቁጥር 058 440 09 13 ደውለው መጠየቅ ችላሉ፡፡

የእብናት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here