የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለቢሮ አገልግሎት የሚዉሉ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃ እና ለሲኦሲ መመዘኛ የሚሆን ጥሬ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሎት መግዛት ይፈልጋል፡፡ እንዲሁም አሮጌ ቆርቆሮዎች እና ቁርጥራጭ ብረቶችን አወዳድሮ መሽጥ የፈልጋል፡፡ በመሆኑም ሎት 1. ለአዉቶ ሞቲቭ፣ ሎት 2. ማኑፋክቸሪንግ፣ ሎት 3. ኤሌክትሪክሲቲ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 4. ኮንስትራክሽን፣ ሎት 5. አይሲቲ፣ ሎት 6. ቴክስታይል ጋርመንት፣ ሎት 7. ስቴሽነሪ፣ ሎት 8. የጽዳት እቃ፣ ሎት 9. የደንብ ልብስ፣ ሎት 10. ሮድ ኮንስትራክሽን እና ሎት 11. ዉድ ወርክ እንዲሁም አሮጌ ቆርቆሮዎች እና ቁርጥራጭ ብረቶችን ከላይ ለተጠቀሱት አገልግሎት የሚዉል ጥሬ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና መሸጥ ይፈልጋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥዉ መጠን ብር 100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር) እና በላይ የሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና የሥራ ዝርዝሩን ዓይነት ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ዉድድሩ በነጠላ ድምር ዋጋ ሆኖ አሸናፊ የሚለየው በሎት ወይም ጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ የሚሆን ለሚገዙት አሸናፊ ይሆናል፡፡ ለሚሸጡት አሮጌ ቆርቆሮ እና ቁርጥራጭ ብረት ግን በድምር ከፍተኛ የሞላዉ አሸናፊ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎችን በራሳቸው ወጭ በማጓጓዝ በሙያተኞች እየተረጋገጠ ዕቃዎችን ገቢ ያደረጋል፡፡
- የጨረታ ተወዳዳሪዎች በሌሎች ተወዳዳሪዎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የለበትም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የሞሉትን የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ወይም ገጽ ላይ ፊርማ እና የድርጅቶች ማህተም በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግዥና ፋ/ን/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ 2፡30 እስከ 11፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ የሚቆይበት ጊዜ ከታህሳስ 6/2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም ሲሆን ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም እሰከ ጠዋቱ 3፡00 ድረስ ተጫራቾች ሰነዳቸውን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡05 ታሽጎ ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነድ መሸጫ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለሚሸጡ አሮጌ ቆርቆሮዎች መነሻ ዋጋ ሙሉ ቆርቆሮ መነሻ ዋጋ ብር 400 (አራት መቶ ብር) እሩብ ጉዳይ መነሻ ዋጋ 1/3 ብር 250 (ሁለት መቶ ሃምሳ ብር) ግማሽ ቆርቆሮ መነሻ ዋጋ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) እና ቁርጥራጭ ብረት ለ1 ኪሎ መነሻ ዋጋ ብር 70 (ሰባ ብር) መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ለአሮጌ ቆርቆሮዎች ማስያዣ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የሞሉትን የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሰፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ለቁርጥራጭ ብረት ማስያዣ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር 60,000 (ስልሳ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ የሚፈልጉ ግዥና/ፋ/ን/አስ ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 111 83 60 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

