ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
97

በሰሜን ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የባ/ዳር ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የባ/ዳር/ዙ/ወ/ መንገድ ትራንስፖርት ሴክተር ጽ/ቤት ሎት1. የስላቨ ካልቨርት የግንባታ ስራ ከይጎማ 2ቱ ቤተማሪያም እና ከጉብሪት እስከ  ፈረስ ወጋ ባለው የመንገድ ፕሮጀክት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ እና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፤ ተከታታይ የፋክቱር ቁጥር ያላቸው፡፡
  4. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣በድልድይ ስራ መልካም የስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የግንባታው ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የጠቅላላ ዋጋውን5 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በባ/ዳር/ዙ/ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ፋ/አስ/የስራ ሂደት መረጃ ዴስክ ዘወትር በስራ ሰዓት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመረጃ ዴስክ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21 ተከታታይ ቀናት ከፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ22 ኛው ቀን 3:30 ታሽጎ በ4:00 ይከፈታል፡፡ እለቱ ህዝባዊ ባዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ ቀን በ4:00 ጨረታው ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ተጫራቾች ያሸነፉትን ግንባታ ትራንስፖርት ወጭ በመሸፈን የሚያደርሱ መሆን አለበት፡፡
  12. ግዥው በጥቅል ይፈፀማል፤ ስለሆነም ሁሉም ዋጋዎች መሞላት አለባቸው፡፡
  13. መ/ቤቱ በየሎቱ እየከፋፈለ የመጣውን ማስታወቂያ ዝርዝር ግዥ ለመፈፀም መቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው::
  14. የጨረታ ሰነዱን መሰረዝና መደለዝ ከውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
  15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስሰ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 5 2 02 በመደወል ማግኘት ይቻሳል፡፡
  16. በሰነዱ ላይ ያልተገለጹ ቢኖሩ በግንባታ ግዥ መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

የባህር ዳር/ዙ/ወ/ ገንዘብ /ጽ/ቤት

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here