በአብክመ በሰ/ጎጃም ዞን የይ/ዴ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ ቤት ለይ/ዴ/ወ/ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ ሎት1. የጸዳት ዕቃዎች ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ እና የይ/ደ/ወ/ መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት የመንገድ ጥገና ማለትም ሎት2. ከደብረማዊ እስከ ይዞራ ቀበሌ እና ሎት3. ከሞሰቦ እስከ ሰንቀኛ እና ዋልካ ቀበሌ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማስጠገን ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የቲን ተመዝጋቢ መሆናቸዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በዘርፉ አግባብ ያለዉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጸዳት ዕቃዎች ግዥው ከ200‚000 ብር (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው የመንገድ ጥገናዉ ከደረጃ 7 እና ባላይ ያሉ ሆነዉ በመንገድ ስራ ልምድ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ተጨማሪ ማስረጃ ቢያስፈልጋቸዉ የይ/ዴ/ወ/ገ/ኢ/ትብ/ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 ወይም በስልክ ቁጥር 058 33 80 298 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ሂሳብ የጸዳት ዕቃዎች 8000 (ስምንት ሽህ ብር) እና የመንገድ ጥገናዉ ከደብረማዊ እስከ ይዞራ ቀበሌ 82500(ሰማንያ ሁለት ሽህ አምስት መቶ ብር ብቻ) እና ከሞሰቦ እስከ ሰንቀኛ እና ዋልካ ቀበሌ 35000 ( ሰላሳ አምስት ሽህ ብር) ብቻ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ከዋና ገንዘብ ያዥ አስይዘዉ ለግዥ ኦፊሰሮች ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከሆነ ከፖስታ ዉስጥ አስገብተዉ ማሸግ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ካለ ከአሸናፊዉ ዋጋ ጋር ተደምሮ ሲያዝ የተሸነፈዉ ተጫራች የሚያስይዘዉ ገንዘብ ይመለስላቸዋል፡፡
- ጨረታዉ የሚከፈትበት ዕለት በበዓል ቀናት ከሆነ ወደ ቀጣዩ የስራ ቀን ይሸጋገራል፡፡
- የጸዳት ዕቃዉ ጨረታ ሰነዱን ከታሕሳስ 6/2018 ዓ.ም ዓ.ም እስከ ታሕሳስ 27/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት እና የመንገድ ጥገና ጨረታ ሰነዱን ከታሕሳስ 13/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 3/2018 ዓ.ም ለ21 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ታትሞ የሚቆይ ሲሆን የተሞላበትን ፎርም ቲን፣ የንግድ ፈቃድዎንና ሌሎች ያልተጠቀሱ ማስረጃዎችን በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የፅዳት ዕቃዉ ጨረታዉ የሚዘጋበት ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም በ3፡30 ሲሆን ጨረታዉ የሚከፈተው ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም በ4፡00 ቢሮ ቁጥር 3 ፍላጎት ያለዉ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ በተገኙበት ይከፈታል እና የመንገድ ጥገና ጨረታዉ የሚዘጋበት ጥር 4/2018 ዓ.ም በ3፡30 ሲሆን ጨረታዉ የሚከፈተዉ ጥር 4/2018 ዓ.ም በ4፡00 ቢሮ ቁጥር 3 ፍላጎት ያለዉ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ወኪሉ በጨረታዉ መክፈቻ ዕለት ባይገኙ መ/ቤቱ ጨረታዉን ለመክፈት የሚገድበዉ የለም፡፡
- አሸናፊ አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ 10በመቶ የዉል ማስከበሪያ በማስያዝ ዉል መያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች አሽገዉ ከሚያስገቡት ሰነድ እና ፖስታ ላይ አድራሻና የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡
- ተጫራቾቹ በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ጨረታዉን የምናወዳድረዉ በሎት ወይም በጠቅላላ ዋጋ ነዉ፡፡
- ግዥ ፈጻሚ አካል ያሸነፈውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ እንዳስፈላጊነቱ 20በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- የሚሞላው ዋጋ ማንኛውንም ታክስ ያካተተ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታዉ ለ40 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
- የጸዳት ዕቃዎች ጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት 200 (ሁለት መቶ) ብር ብቻ ነዉ፡፡
- የመንገድ ጥገና ጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት 400 (አራት መቶ ብር) ብቻ ነዉ፡፡
የይልማና ዴንሳ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

