ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
48

የዳባት/ቴ/ሙ/ማ/ ኮሌጅ የተለያዩ የስልጠና ቁሳቁሶችን 1.አላቂ የጽዳት እቃዎች፣2.አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎ፣3.ለጥበቃ አገልግሎት የሚውሉ የደንብስ ልብስ፣4. አላቂ የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች፣5. ቋሚና አላቂ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች፣6. ቋሚና አላቂ የግብርና ቁሳቁሶች፣7. ቋሚና አላቂ የፈርኒቸር ቁሳቁሶች፣8. ቋሚና አላቂ የአውቶሞቲቭ ቁሳቁሶች፣9. ቋሚና አላቂ የሆቴል ቱሪዝም ቁሳቁሶች፣10.ቋሚና አላቂ የጋርመንት ቁሳቁሶች፣11. ቋሚና አላቂ የህንፃ መሳሪያዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የዘመኑ ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር ቲን  ያላቸው፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  4. የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ የኢትዮጵያ 200 ብር ብቻ በመግዛት መውሰድ ይችላል፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትፈልጉ የጨረታ  ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከታህሳስ13/2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 27/2018/ዓ. ከዳ/ቴ/ሙ/ማ/ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 4 ዘወትር በተከታታይ የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተመሰከረ ቸክ ወይም ሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ዳ/ቴ/ሙ/ማ/ ኮሌጅ ግዥ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ወይም ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም፡፡ በተጨማሪም ያስያዙት  ጥሬ ገንዘብ ከተሞላው ጠቅላላ ዋጋ ድምር ሁለት በመቶ ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቾች ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
  7. የጨረታ ሰነድ ገቢ የሚሆንበት የመጨረሻ ቀን ታህሳስ 4/2018 ዓ.ም 4፡00  የሚጠናቀቅ ሲሆን የሚከፈትበት ቀን ታሕሳስ 28/2018 ዓ.ም 4፡15 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፤ይከፈታል ባይገኙም በዳቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 በይፋ ይከፈታል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በተናጠልም ሆነ በጥቅል ዋጋ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች ታይቶ ኮሌጁ የሚያዋጣውን ይመርጣል፡፡
  9.  ተጫራቾች በእያንዳንዱ በገዙት ሰነድ ላይ የዘረዘሩትን የስራ አይነቶች ሙሉ በሙሉ በመሙላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
  10. አሸናፊው ያሸነፈባቸውን ቁሳቁሶች ኮሌጁ ድረስ አምጥቶ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  11.  ኮሌጁ ስለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12.  ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 63 93 89 26/ 09 45 56 64 72 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የዳባት /ቴ/ሙ/ማ/ ኮሌጅ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here