ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
59

በደቡብ ጎንደር ዞን አዲስ ዘመን ማረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት የህግ ታራሚዎች ምግብ  እና ምግብ ነክ የሚውሉ ሎት1. ጤፍ ፣በቆሎ ሩዝ፣ ሎት2. የባቄላ ክከ፣ ተቀምሞ የተፈጨ በርበሬ ፣ ሎት3. የዳቦ ፊኖ ዱቄት፣ ሎት4. የዳቦ ማንኳፈፊያ፣  የምግብ ጨው፣ ሎት5.የምግብ ዘይት፣ሎት6.የማገዶ እንጨት፣ በግልጽ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የንግድ ፍቃድ የምስክር ወረቀት (የቲን) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  3. የመግዛት አቅም ከ200‚000 ብር እና በላይ ለሆናችሁ አቅራቢዎች የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናችሁ መረጃ ማቅረብ የምትችሉ፡፡
  4. ከ1-3 የተዘረዘሩትን መረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ የእያንዳንዱን ሎት ለየብቻ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ካቀረቡት የመጫረቻ ዋጋ ሎት1. 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፣ ሎት2. 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ) ፣ሎት3. 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር)፣ ሎት4. 2‚500 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) ፣ሎት 10,000 (አስር ሺህ ብር)፣ ሎት6. 10,000 (አስር ሺህ ብር) በሲፒዮ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማቅረብ ደረሰኝ በማስቆረጥ ኮፒውን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. የውል ማስከበሪያ ቢል ቦንድ ያሸነፉበትን ዕቃ ግዥ ዋጋ 10በመቶ በመቶ በሲፒዮ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከታተመበት ቀን ጀምሮ ከታሕሳስ 13/ 2018 ዓ.ም  እስከ ታሕሳስ 28 /2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የመጫረቻ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት 100.00 (አንድ መቶ) ብር  ግ/ፋ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ እስከ 11፡30  ድረስ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ፡፡
  8. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ቅጽ ላይ የሞሉትን ዕቃ ግዥ ስፔስፊኬሽን እና ነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል ያለምንም ስርዝ ድልዝ ተሞልቶ በቀን 28/4/ 2018 ዓ.ም ዓ.ም ከጠዋቱ እስከ 3፡25 ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ ዕለት በ3፡30 ላይ ይታሸጋል በዚሁ እለት 4:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የከፈታል፡፡
  9. የጨረታ ማስታወቂያው ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ስለሆነ በሎቱ የተጠየቀው ዕቃ፣ ሁሉም በትክክል መሞላት አለባቸው፡፡ አሸናፊዎች የሞሉት ዕቃ ዋጋ እያንዳንዱ ዋጋ ጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ነው፡፡
  10. የጨረታው አሸናፊ የአሸናፊነት ጥሪው ከደረሰው ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በአሸነፉበት የመጫረቻ ዋጋ መሰረት የውል ማስከበሪያውን በማስያዝ ውል መውሰድ ይችላል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. በዕቃ ወይም አገልግሎት ግዥው ላይ አሳማኝ ምክንያቶች ካሉ እና መ/ቤቱ ካመነበት እስከ 20በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
  13. ከላይ በሎት ምድብ የተጠየቁት ግዥዎች አቅርቦት ወጪ በአቅራቢው ሲሆን አ/ዘመን ማረ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  14. ለበለጠ መረጃ በቢሮ ስልክ 058 44 40 031/ 058 44 40 971/0948813948/0918441428 በመደመል መረዳት ይቻላል፡፡
  15. የጨረታ መክፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡

የአዲስ ዘመን ማረ/ቤት አስ/ጽ/ቤት

 

 

 

 

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here