ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
45

የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ባህር ዳር ቅርንጫፍ አንድ ኮስትር ወይም ተመሳሳይ መኪና የመቀመጫ ወንበር ከ27 እስከ 30 ሰዎችን የመያዝ አቅም ያለው ባስ ተሽከርካሪ በግልዕ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ አመት ለሰራተኞ መከራየት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የቲን ሰርተፊኬት፣ ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከታህሳስ 13/04/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 3/2018 ዓ.ም ለ21 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ይቆያል፡፡ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡40 ባህርዳር ከተማ ጣና ሀይቅ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው መ/ቤት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አገልግሎት መ/ቤታችን በአካል በመቅረብ 300 ብር በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድቦንድ) ለሚወዳደሩበት የሰርቪስ አገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ሁለት በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. የዋጋ ማቅረቢያቸዉን እና የጨረታ ማስከበሪያዉን በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው በአገልግሎት መ/ቤቱ የግዥ መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  7. የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ዉስጥ የጠቅላላ ዋጋዉን 10በመቶ የዉል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ዉል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
  8. የሰርቪስ አገልግሎት ማቅረቢያ ጊዜ ቢያንስ እስከ አንድ አመት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ ይቆያል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 226 51 52 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

መድሃኒት አቅራቢ አገ/ባሕ/ቅርንጫፍ

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here