ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
63

በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ/ሲ/እ/ወ/ ገንዘብ /ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ 1.ስሚንቶ፣ 2. የውሃ እቃዎች፣ 3. ፓምፕ አቅርቦት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን (ቲን)ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ ለእያንዳንዳቸው በመግዛት የጨረታ ሰነዱን ከመ/ቤታችን ረዳት ገንዘብ  ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለተ.ቁ 1. 13000 (አስራ ሶስት ሽህ ብር)፣ ለተ.ቁ 2.100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር)፣ ተ.ቁ 3. 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዛ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዝብ ገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ ገ/ጽ/ቤት ግዥና  ንብረት አስተዳደር ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማለትም ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በስራ  ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገንዘብ/ጽ/ቤት ኃላፊ ቢሮ ቁጥር 1 በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 3፡30 ታሽጐ 4፡00  ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች በጨረታው ያወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን የማይወስድ መሆኑ ማወቅ ይኖርበታል፡፡
  11. አሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፈባቸውን እቃዎችን ወረዳው ድረስ በራሱ ትራንስፓርት ወጭ ማቅረብ የሚችልና ለፍትህም ሆነ ለማንኛውም አገልግሎት የሚከፈለውን ወጭ በራሱ የሚችል፡፡
  12. መ/ቤቱ ጨረታ አሸናፊውን በጥቅል ዋጋ  ይለያል፡፡
  13. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ አቤቱታ ካላቸው በተከታታይ 5 የስራ ቀናት ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን፤ ከ 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውጭ የመጣ ቅሬታ ጽ/ቤቱ የማይቀበል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  14. መ/ቤቱ ከአሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፍቸውን እቃዎች 20በመቶ ከውል በፊት የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. እቃዎች በባለሙያ እንደተረጋገጡ ርክክብ  የሚፈፀም ይሆናል፡፡
  16. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓላት፣ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  17. አሸናፊው ድርጅቱ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ከ5 የስራ ቀናት በኃላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ መጥቶ ውል በመያዝ የውል ማስከበሪያ 10በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  18. ከአሸናፊው ድርጅት ሶስት በመቶ የቅድመ ግብር የሚቆረጥ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  19. ግዥ ፈጻሚው አካል ግዥውን ለመገምገም ፣ለማጽደቅ ፣አቤቱታ ቢነሳ ለማስተናገድ እና ከአሸናፊ ድርጀቱ ጋር ውል እስከሚገባ ድረስ የመጫረቻ ሰነዱ ጸንቶ የሚቆየው ለ40ቀን ይሆናል፡፡
  20. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 66 40 464/ 002 በመደወል ዝርዝር መረጃውን ማግኘት ይቻላል፡፡

ጎንቻ /ሲ/እ/ወ/ ገንዘብ /ጽ/ቤት

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here