ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
40

ደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት በEASE PROJECT የተያዘውን እቅድ ለመፈፀም አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ እና አላቂ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ጥቅል ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ በዚህ መስርት፡- 1. የህንጻ መሳሪያ፣ 2. የኤሌክትሮኒክስ እና የኮምፒዩተር እቃዎች፣ 3. የጽዳት እቃዎች፣ 4. የቤት እና የቢሮ እቃዋች፣ 5. የፈርኒቸር እቃዎች፣ 6. የኤሌክትሪክ እቃዎች እንዲሁም 7. የግብርና ዕቃዎች ለመወዳደር የምትፈልጉ የመወዳደሪያ ሰነዱን ከመስሪያ ቤታችን ቢሮ ቁጥር 02 የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን እንድትገዙ እና የምትሸጡበትን ዋጋ በመሙላት እና በታሸገ ፖሰታ በማደርግ ኮሌጁ ቢሮ ቁጥር 02 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን እንድታስገቡ እየገለጽን፡-

  1. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት 11፡30 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይ እና በዚሁ ሰዓት ይታሸጋል፡፡
  2. ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ተጫራቾች  ወይም  ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 02 የከፈታል፡፡ በእለቱ  ካልተገኙ ግን  ጨረታው  በኮሚቴ ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የህዝብ በዓል ወይም በእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ህንፃ መሳሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር)፣ ኤሌክትሮኒክስ እና የኮምፒተር እቃዋች ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር)፣ የጽዳት እቃዎች ብር 2,000 (ሁለት ሺህ ብር)፣ የቤት እና የቢሮ እቃዎች ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር)፣ የፈርኒቸር እቃዎች 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) እንዲሁም የኤሌክትሪክ እቃዎች ብር 8000 (ስምንት ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ በማስያዝ ከጨረታ ፖስታ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድና የሥራ ፈቃድ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ከመጫረቻ ፖስታው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የመጫረቻቸው ጠቅላላ ዋጋ ብር 200000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር ) እና በላይ ከሆነ (የቫት) ሰርተፊኬት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች ኮሌጁ በአዘጋጁ የጨረታ ሰነድ ላይ የእቃውን ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከተቀመጠው ስፔስፊኬሽን ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም፡፡
  7. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ መመሪያ የመገዛት ግዴታ አለባቸው፡፡
  8. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. አሸናፊው የሚለየው በሎት /በድምር/ ዋጋ ነው፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ ከታች በስልክ ቁጥር 058 771 26 32 /058 771 /058 771 71 24 /058 771 50 28 /058 771 71 69 /058 771 70 27 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here