በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ 2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ 3 የፅዳት ዕቃዎች፣ 4 ኢምፖርትድ ፈርኒቸር፣ 5 የመኪና ጎማ ከነ ካላማዳሪው እና 6 የስፖርት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከአዊ ብሄ/አስ/ዞን የእን/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ጨረታው በወጣበት በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 08 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ የሚለየው በሎት ዋጋ ይሆናል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 08 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 227 12 58 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት