ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
45

የደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለማስተማሪያ አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ጥቅል ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት፡- 1. የህንጻ መሳሪያ ዕቃዎች፣ 2. የኤሌክትሮኒክስ  እና የኮምፒዩተር ዕቃዎች፣ 3. የመኪና ዕቃዎች፣ 4. የግብርና ዕቃዎች፣ 5. የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ 6. የጽህፈት መሣሪያ፣ 7. የጋርመንት ዕቃዎት፣ 8. የሞባይል ዕቃዎች እንዲሁም 9. የጽዳት ዕቃዎች ሲሆኑ ለመወዳደር የምትፈልጉ የመወዳደሪያ ሰነዱን ከመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 2  የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ገዝታችሁ በመውሰድ  የምትሸጡበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ኮሌጁ ቢሮ ቁጥር 2 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን እንድታስገቡ እየገለጽን፣

  1. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በዚሁ ሰዓት ይታሸጋል፡፡
  1. ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል፡፡ በእለቱ ካልተገኙ ግን ጨረታው በኮሚቴ ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የህዝብ በዓል ወይም በእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  2. ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ለህንጻ መሳሪያ ብር 10,000 ብር፣ የኤሌክትሮኒክስና የኮምፒዉተር ዕቃዎች ብር 8,000 ብር፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ብር 10,000 ብር፣ የመኪና እቃዎች ብር 5,000 ብር፣  የግብርና ዕቃዎች ብር 20,000 ብር፣ የጽህፈት መሣሪያ ብር 10,000 ብር፣ የጋርመንት ዕቃዎች ብር 10,000፣  የሞባይል ዕቃዎች ብር 10,000 የጽዳት ዕቃዎች ብር 3,000 በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ በማስያዝ ከጨረታው ፖስታ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድና የሥራ ፈቃድ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ከመጫረቻ ፖስታው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የመጫራቻቸው ጠቅላላ ዋጋ ብር ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ (የቫት) የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ አለበቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ኮሌጁ በአዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የእቃውን ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከተቀመጠው ስፔስፊኬሽን ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም፡፡
  6. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ መመሪያ የመገዛት ግዴታ አለባቸው፡፡
  7. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. አሸናፊዉ የሚለየዉ በሎት /በድምር ዋጋ/ በሞሉት ነዉ፡፡
  9. ለበለጠ መረጃ ከታች በስልክ ቁጥር 058 771 26 32 /058 771 /058 771 71 24 /058 771 50 28 /058 771 71 69 /058 771 70 27 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here