ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
47

በምሥራቅ ጎጃም ዞን በአዋበል ወረዳ የሚገኘዉ የወጀል ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወጀል ከተማ የከተማ ቦታን በሊዝ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ቦታ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ  ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ  አንቀፅ 1  በፊደል ተራ ከ”ሀ” እስከ “ሠ” በተዘረዘረው መሰረት ለመኖሪያና ለንግድ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

  1. የጨረታ ቁጥር ወጀል/01/2018
  2. የጨረታ ዙር 1ኛ
  3. የጨረታ ዓይነት መደበኛ
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ደረጃዉን በጠበቀ ፖስታ በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያ የገቢ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ እና በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) የሞሉበትን ዋጋ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. የጨረታ ሰነድ የወጀል ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ጋዜጣዉ በወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡
  8. የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻለዉ ጋዜጣዉ ከወጣበት ቀን እስከ 10ኛዉ ቀን ከቀኑ 9፡00 ድረስ ይሆናል፡፡ ስለሆነም በዚሁ ቀን ከቀኑ 10፡30 የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸግ ይሆናል፡፡
  9. ጨረታዉ የሚከፈትበት ጨረታዉ በጋዜጣ ከሚያበቃበት ቀን በነጋታዉ 11ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ሲሆን ተጫራቾችም ሆነ ወኪሎቻቸዉ ባይገኝም እንኳ ጨረታዉ በእለቱ ወጀል ከተማ መሪ ማ/ቤት ቅጥር ግቢ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
  11. የተጫራቾች ሰነድ ሥርዝ ድልዝ የሌለበትና ተነባቢ መሆን ይኖርበታል፡፡
  12. በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  13. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  14. ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
  15. ስለጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የወጀል ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here