ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
82

የባሕር ዳር እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናት ምርመራ ላብራቶሪ ለሚገዛቸው ዕቃዎች ሎት 1.  የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ ሎት 2. የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3 ኮምፒውተርና ላፕቶፕ እቃዎች፣ ሎት 4  የህንፃ መሣሪያዎች፣ ሎት 5. አመታዊ የኮምፒወተር ጥገና ሰርቪስ እንዲሁም ሎት 6. የተለያዩ ኬሚካሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን  መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፋ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ሊሆኑ ይገባል ሌሎች ያልተጠቀሱ ቢኖሩ በመንግስት የግዥ መመሪያ በሚፈቅደው ተፈጻሚነት ይኖርዋል፡፡
  2. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዘጋቢ መሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን እቃ ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡ ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም፡፡
  7. አሸናፊው ማሸነፋ ከተገለፀበት ከ5ኛው ቀን በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው እለት 4፡00 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በመሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. መ/ቤቱ 20 በመቶ የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አሽናፋው የሚለየው በጥቅል ሎት ድምር ነው፡፡
  11. ተጫሪቾች ለሚጠየቁት የዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
  12. ለበለጠ መረጃ በሥልክ ቁጥር 058 226 54 93 ወይም እንስሳት ላብራቶሪ በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የባ/ዳር እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርመራ ላብራቶሪ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here