ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
65

በምሥራቅ ጎጃም ዞን በአነደድ ወረዳ የአምበር ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2018 በጀት ዓመት በከተማዉ ዉስጥ ለዉስጥ ያለውን መንገድ ለማሰራት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የማሽነሪዎች ኪራይ ይፈለጋል፡፡ 1. ግሬደር፣ 2. ኤክስካቫተር፣ 3. ሮሎ፣ 4 .ገልባጭ፣ 5. የውሀ ቦቲ (ሻወር ትራከ) እንዲሁም 6. ዶዘር ሲሆኑ እነዚህን ማሽነሪዎች ማከራየት የሚፈልጉ   የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳድር ትችላላችሁ ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የኪራይ መጠን ከብር 200‚000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ስሌት ታክስ (ቫት) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላልሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል አ/ ከ/መሪ ማ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች ኦርጅናል የጨረታ ሰነድና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአንድ ፖስታ፣ ኮፒ የጨረታ ሰነድ በአንድ ፖስታ በማድረግ ሁለቱን ፖስታዎች በአንድ ፖስታ በጥንቃቄ አሽገው የድርጅቱን ህጋዊ ማህተምና አድራሻውን በመሙላት ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ በአነደድ ወረዳ በአምበር ከተማ መሪ ማ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ ዕለት 3፡30 ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡00 ላይ በአነ/ወ/አ/ከ/መ/ማ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል፡፡  21ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙ ጨረታውን ከመክፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑ በተጨማሪ በጨረታው ሂደት ያልተገኙ ተጫራቾች በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  8. በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚይዝበት ወቅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፉትን ንብረት ጠቅላላ ወጭውን በመሸፈን አነደድ ወረዳ አምበር ከተማ  ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  10. ውድድሩ በጠቅላላ ዋጋ (በሎት ውድድር) ነው፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ ከቀረበው አጠቃላይ የስራ መጠን /ዋጋ ላይ እስከ 20 በመቶ መቀነስ እና መጨመር ይችላል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በክፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ አ/ከ/መሪ/ማ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 261 00 12 መረጃ መግኘት ይችላሉ፡፡

            የአምበር ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here