ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
51

ምሥራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ ፍ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ለ2018 በጀት አመት ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 ቋሚ  እቃዎች፣ ሎት 3 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 4 የህትመት ውጤቶች፣ ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ እቃዎች ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. በ2018 ዓ.ም በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃዎች ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግዥ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች ከብር 200,000 (ከሁለት መቶ ሺህ ብር) በታችም ጠቅላላ ዋጋ ቢሆን የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢነት አብሮ ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመስከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር እያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከ1-5 ሎት ድረስ ከማቻ/ወ/ፍ/ቤት ቢሮ ቁፐር 16 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት አንድ በመቶ 1-5 ላሉት ሎቶች በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት 11፡00 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በቻ/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/አስ/ቢሮ ቁጥር 16 በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስወቂያ በጋዜጣ ከወጣት ቀን ጀምሮ በ16 ተኛው ቀን እስከ 2፡59 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 3፡00 ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች በተገኘበት ይታሽጋል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማቻ/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 16 በ16ኛው ቀን 3፡30 ጀምሮ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ፖስታው ከመክፈት የማይስተጓጉለው መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  9. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በዓል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊ መሆን የሚቻለው በሎት ወይም በነጠላ ዋጋ ዝቅተኛ ያቀረበ ተጫራች መሆኑ ታውቆ የሁሉም እቃዎች ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ እና ዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ስም ፊርማ እና ማህተም መደረግ ይኖርበታል፡፡
  11. መ/ቤቱ ከተዘረዘረው ግዥ መጠን 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  12. አሸናፊው ከጠቅላላ ዋጋው ውስጥ 10 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. አሸናፊው ድርጅት እቃውን በራሱ ትራንስፖርት ማቻ/ወ/ፍ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
  15. ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፡፡
  16. አሸናፊው ድርጅት በስማቸው የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ በስክ ቁጥር 09 18 21 02 65 ደውለው መጠየቅ ችላሉ፡፡

የማቻከል ወረዳ ፍ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here