የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት አመት በመደበኛ በጀት ለት/ቤቱ የሚስፈልጉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1 ለምግብ አገልግሎት የሚዉል የተዘጋጀ በርበሬ፣ የተዘጋጀ ሽሮ፣ አተር ክክ፣ ምስር ወዘተ፣ ሎት 2 የእርድ ስጋ፣ ሎት 3 አትክልት፣ ሽንኩርት፣ ድንች፣ እንቁላል ወዘተ እንዲሁም ሎት 4 ማገዶ እንጨት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ግዥው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የእቃዎችን አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታ ሰነዱን ከቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ወይም በባንክ በተመሰረተ (ሲፒኦ) ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ግ/ን/አ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ እለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ካልሆነ ወደ ቀጣዩ የሥራ ቀን ይተላለፋል፡፡
- ጨረታው በእያንዳንዱ ፍላጎት በተናጠል ዋጋ ነው፡፡
- አሸናፊው በገባው ውል መሰረት እቃዎችን እስከ ተቋሙ ንብረት ክፍል ድረስ የማድረስ ግዴታ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 08 ድረስ በአካል በመገኘት በስልክ 033 111 46 84 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት

