ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
100

የሻሁራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ  ማለትም ሎት 1 የደንብ ልብስ፣ ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 3 አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ሎት 5 የተለያዩ ህትመቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃስን፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. በዘርፍ ህጋዊ የታደሰ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  3. የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥ መጠን ከ100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመስከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የጨረታ አይነትና ዝርዝር መግስጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመስስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመገዛት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በአለፋ ወረዳ በሻውራ /የመ/ደ/ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 7 በመገኘት ሰነዱ መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቮሎፕ በማድረግ የሻ/የመ/ደ/ ሆስፒታል ቢሮ በዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ከመክፈቻ ቀንና ስዓት በፊት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ ክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባችሁ፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ኦርጅናሉንና ኮፒውን በሁለት በታሸገ ኢንቨሎት ፖስታ በጥንቃቄ ተሞልቶ በሻሁራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከ09/03/2017 ዓ.ም እስከ 23/03/2017ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በአየር ላይ ቆይቶ በቀን 23/03/2017 በ11፡00 የጨረታ ሳጥኑ ይታሸግና በቀን 24/03/17 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሻ/የመ/ደ/ሆስፒታል 3፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ዕለት ህዝባዊ በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተባለው ስዓት ይከፈታል፡፡
  11. አሸናፊ ድርጅቱ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ5 የሥራ ቀናት የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ በማቅረብ ውሉን መፈፀም ይኖርበታል፡፡ በተባለው ቀን መጥቶ ውሉን የማይፈፅም ከሆነ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይሆንና ለሁለተኛው አሸናፊ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
  12. በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች ተገቢውን የጨረታ ማስከበሪያና አሸናፊ ከሆኑ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  13. የጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች እቃውን በራሱ ትራንስፖርት ሻሁራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ በማምጣት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ እቃው ገቢ የሚሆነው በባለሙያ እየታየ ትክክል መሆኑንና መስራቱን ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡
  14. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈስጉ በሻ/የመ/ደ/ሆስፒታል  ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 09 18 21 27 03 ወይም 09 18 41 90 47 መደወል ይችላሉ፡፡
  16. ተቀባይነት የሌላቸው ተመላሽ የሚሆኑ እቃዎች ትራንስፖርት ወጭ በአቅራቢው በራሱ የሚሸፈን መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል፡፡
  17. የሚያቀርቡት ዶክሜንት ጥራቱን የጠበቀ፣ ሥርዝ ድልዝ የለለውና የሚነበብ መሆን አለበት፡፡
  18. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- አሽናፊው የሚለየው በሎት ወይም ድምር ነው፡፡

የሻሁራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here