በምሥራት ጎጃም አስተዳደር ዞን የደብረ ኤልያስ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 3 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 4 የህትመት እቃዎች እና ሎት 5 የዉጭ ስሪት ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች በዘርፉ ከተሰማሩ ነጋዴዎች መካከል የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ያላቸዉ እና ጨረታው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ፡-
- በዉድድሩ መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛዉ ቀን ከደ/ኤ/ወ/ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመቅረብ የተዘጋጀውን የእቃ ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ ብር 20 (ሃያ ብር) የማይመለስ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ይዘጋና በእለቱ የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በጽ/ቤቱ ግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 በግልጽ ይከፍታል፡፡
- ተጫራቾች በሞሉት የጨረታ ዋጋ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ የጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ መሂ 1 ደረሰኝ ወይም በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት አሽናፊነቱ ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለበት ውል ሲይዝ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በመ/ቤቱ መሂ 1 ደረሰኝ ወይም በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበት የጨረታ ሰነድ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም እና አድራሻ በመሙላት የንግድ ፈቃድ የቲን ነምበር ምዝገባ፣ የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት በማስያዝ እስከ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት በ16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ይከፈታል፡፡ በተጫራቾች የሚቀርበዉ የመወዳደሪያ ዋጋ ለ30 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ ከሚገዛዉ እቃ ላይ 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ በሚያስቀምጠው አይነት ወይም ስፔስፊኬሽን መሰረት ሰነዳቸዉን ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች ደ/ኤ/ወ/ፍ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በራሳቸዉ ውጭ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ ተጫራቾች የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 250 00 59 ወይም 058 250 03 33 ደዉለዉ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሎት ወይም በጠቅላላ ድምር አሸናፊዉ የሚለይ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ሲሞላ ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ ነገር ግን ካለበት ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
የደብረ ኤልያስ ወረዳ ፍ/ቤት

