የምዕራብ ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የሠከላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን ለወረዳችን ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ እቃዎችን ማለትም ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 2 ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታዉ ለመወዳደር የምትፈልጉ ድርጅቶች፡-
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ የግዥና መክፈያ መለያ ቁጥር (ቲን) እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ሰከላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 20,000 (ሃያ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በጽ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በመቁረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታዉ ፖስታ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሁኖ ይቆይና በ16ኛዉ ቀን ከረፋዱ 3፡30 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በሰከላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አጥር ግቢ ዉስጥ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋበት በ16ኛዉ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተባለዉ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱ ከተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት ዉጭ ዘግይቶ ቢደርስ ተቀባይነት የለዉም፡፡
- አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉበትን እቃ አይነት ከጽ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማንኛዉንም ትራንስፖርት፣ የማጓጓዣ እና የጫኝ አዉራጅ ወጭ ችሉ ማጓጓዝ ማስረከብ አለባቸዉ፡፡
- አሸናፊው የሚለየዉ በጠቅላላ ድምር ሆኖ ከተዘረዘሩት እቃዎች ከፊሉን ብቻ መሙላትና አስተካክሎ መሙላት ሥርዝ ድልዝ ማድረግ ከጨረታ ዉጭ ያስደርጋል፡፡
- ጽ/ቤቱ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ጨረታዉ የሚዘጋጅበት ቋንቋ በአማረኛ ይሆናል፡፡
- ለበለጠ መረጃ ሰከላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 259 00 09 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሠከላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

