ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
64

የእብናት ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ለፍ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 3 ህትመት፣ ሎት4 የደንብ ልብስ፣ ሎት 5 ለቢሮ ጥገና የሚውሉ እና ሌሎች እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድር መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
  4. የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚህ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመሰከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. በሎት የሚገዛውን እቃ አይነትና ዝርዝር መግለ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማገኘት ይችላሉ፡፡ ሆኖም ስፔስፊኬሽን ሳይሞላ ክፍት ያደረገ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
  7. የእብናት ወረዳ ፍ/ቤት በሎት ዘርዝሮ ካቀረባቸው እቃዎች ውስጥ ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ሎት የተዘረዘረውን ሁሉንም ሳይሞላ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
  8. ፍርድ ቤቱ በአጠቃላይ እንዲገዛ ካዘዛቸው እቃዎች ላይ 20 በመቶ የመጨመር እና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ፍርድ ቤቱ ተጫራቾችን በእያንዳንዱ ሎት በተናጠል ዋጋ የሚያወዳድር ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን መግዛት ይችላሉ፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚወዳደረበት ብር የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግ/ን/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  13. ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከታህሳስ 13/2018 ዓ.ም እስከ  ጥር 02/2018 ዓ.ም በ20 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ በ21ኛው ቀን ጥር 03/2018 ዓ.ም ይከፈታል፡፡ ቀኑ የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 በኋላ ይከፈታል፡፡
  14. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን የሥራ ሂደት 3፡00 በኋላ ይከፈታል፡፡
  15. ፍ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉበ ሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ተጫራቾች ያሸነፏቸውን እቃዎች እብናት ወረዳ ፍ/ቤት ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  17. አሸናፊዎች እንደስፈሳጊነቱ ለ6 ወር ኩንትራት ውል አገልግሎት ሊወስዱ ይችላሉ፡፡
  18. የጨረታው አሸነፊ መሆን የሚችለው በየአንዳንዱ ሎት በተናጥል ዋጋ ዝቅተኛው የዋጋ መጠን የሞላ ነው፡፡
  19. የሚያቀርቡት እቃ ከተጠየቀው (ስፔስፊኬሽን) እና በናሙናው መስረት መሆን አለበት፡፡
  20. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ/ፋ/ን/አስ/ድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 440 00 32 /058 440 01 23 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡

የእብናት ወረዳ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here