ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
94

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ቢሮና ስልጣን ኤጀንሲ ፅ/ቤት/የሰ/ጎ/ፖ/መምሪያ የ2018 በጀት አመት የሚውሉ እቃዎች ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ ሎት 2 የፅዳት ሎት 3 ህትመት ሎት 4. ቋሚ እና አላቂ እቃዎች ሎት 5. የኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 6. የፈርኒቸር ሎት 7 ፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ስለሆነም፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነበር) የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና አግባብ ያለው የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱት የግዥ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ሴት ታክስ ( ቫት) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ
    ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙት የእቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፌኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ ከተጠቀሰው ስፔስፌኬሽን ውጭ ሰርዞ ሌላ ስፔስፌኬሽን መቀየር ከውድድሩ ውጭ ያስደርጋል፡፡
  6. የጨረታ ማስታወቂያው ከ13/04/2018ዐ.ም በሚወጣው በኩር ጋዜጣ መመልከት ወይም ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማዕ/ጎ/ዞ/ፖ/መምሪያ በግ/ፋ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር——በብር 20 ብር/ሀያብር/ በግዥ ባለሙያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሎት ድምር በጥቅል ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 1በመቶበባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በመሂ1 በመቁረጥ ኦርጅናል ጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ይሁን እንጅ በጥሬ ገንዘብ ማስገባት አይቻልም፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም ያስያዙት ሲፒኦ ከ1 በመቶ ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሲሞላ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ
    ፖስታ መ/ቤታችን ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በማዕ/ጎ/ዞ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር ……
    ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት እንደሚችሉ እንገልፃለን፡፡
  10. ጨረታው በአየር ላይ ጸንቶ የሚቆይበት ከታህሳስ 18/2018 ዓ/ም እስከ ጥር 03/2018 ዓ/ም የሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱ ይሸጣል፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕ/ጎ/ዞ/ፖ/መምሪያ በግ/ፋ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር—በጥር 04/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰአት ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
  12. አሸናፊዎች እቃዎችን የሚያስረክቡት በራሳችሁ ድርጅት ይሆናል፡፡
  13. የግዥ መጠን ከ20,000 (ሃያ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ 3 በመቶ ታክስ መክፈል አለበት፡፡
  14. ተጫራቾች በሚያቀርቡበት የመወዳደሪያ ሀሳብ ስማቸውን ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቻን ማስፈር አለባቸው፡፡ የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሎት ወይም በነጠላ በሞላው ዋጋ ሲሆን ተጫራቾች ሁሉንም ዝርዝር ዋጋ መሙላት አለባቸው ያልሞላ ተጫራች ቢኖር ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  15. የጨረታ መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  16. አሸናፊው ተጫራች የእቃዎችን ጥራት በተመለከተ ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች ጥራቱን በማረጋገጥ ማስረከብ ግዴታው ነው፡ በጥራት አረጋጋጭ ባለሙያ መሰረት የጥራት ችግር ያለባቸውን ሙሉ በሙሉ በመመለስ ትክክለኛ ጥራት ያላቸውን እቃዎች የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡ የርክክቡ ቦታ በአሸናፊ ድርጅቱ ይሆናል፡፡
  17. መ/ቤቱ ይህን ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0918151654/0918061424 ደውለው መጠየቅ  ይችላሉ፡፡

የሰሜን ጎን/ዘፐ/ፖ/መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here