ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
77

የማዕ/ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ የወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ባሉት የፑል ንብረት ክፍል ያገለገሉ ዕቃዎች 1. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ኮምፒውተር፣ ፋክስ፣ ላፕቶፕ፣ ፕሪንተር ፤ 2. የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች፣ 3.የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረቶች ፣የተለያዩ መጠን ያላቸው የመኪና ጎማዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ (ድርጅት) በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  2. ተጫራቾች የንብረቶችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200( ሁለት መቶ ) ብር ወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እና በ16ኛው ቀን 4 ድረስ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደርበትን የዕቃ ዋጋ 10 በመቶ (አስር በመቶ) 30,000 (ሰላሳ ሺሕ) ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም ከ60 (ስልሳ) ቀን ያላነሰ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድቦንድ) ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ የገቢ ደረሰኝ የተቆረጠ በጽ/ቤቱ ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን (መጫረቻውን) ዋናውን በጥንቃቄ በ ፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 03 በ16ኛው ቀን 4፡00 ሥዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡15 ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶችን በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ በተገለፀው ቦታ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ንብረቶች ባሉበት ንብረት ክፍል በመሄድ በአካል ማየት ይቻላል፡፡
  8. ጨረታውን አሸናፊ የሚሆነው በተናጠል ይሆናል፡፡
  9. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 118 05 21 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው

የወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here