ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
64

በማከላዊ ጎንደር ታች አርማጭሆ ወረዳ የሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 ዓ.ም ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ 1hz-k79 አንቡላንስ መኪና መለዋወጫ እቃ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

  1. በዘመኑ ታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥው መጠን ብር 100,000 (መቶ ሽህ ብር ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከማጫረቻ ስነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ የመለዋዎጫ እቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ጨረታው ከወጣበት ከታሕሳስ 13/2018 ዓ.ም እስከ ታሕሳስ 27/2018 ዓ.ም ለተከታታይ 15 ቀናት ይቆያል፡፡
  8. የጨረታው ሳጥን የሚታሽገው ታሕሳስ 28/2018 ዓ/ም ከቀኑ 11፡30 ይሆናል
  9. ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ወኪላቸው ባሉበት የሳንጃ የመ/ደ/ሆስፒታል አዳራሽ በታህሳስ 29/2018 ዓ.ም ከጧዋቱ 3፡00 ይሆናል ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ ባይኖሩም የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚወዳደሩበት አንድ በመቶ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሁለት ፖስታ ኦርጀናልና ኮፒውን ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. አሸናፊው ድርጀት በዓ/ህግ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል መውሰድ ይኖርበታል።
  13. ከጨረታ ሰነዱ ላይ ከተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞሉ የዋጋና ሌሎች አላስፈላጊ መረጃዎችን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  14. አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ በከፊል ወይም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን  በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡
  17. የሚያቀርቡት የመኪና መለዋወጫ እቃ ሁሉም እቃዎች ኦርጀናል መሆን አለባቸው፤ ኦርጂናል ለመሆኑ በባለሙያ (በሹፌር) እየተረጋገጠ ወደ ንብረት ክፍል ገቢ ይደረጋል፡፡

ለበለጠ መረጃ 09 18 19 85 88 / 09 39 24 50 07 መደወል ይችላሉ

የሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

 

 

 

 

 

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here